Quality Policy

TEKHAF Trading PLC is dedicated to providing Transport Service and Export and Import products trading that satisfy and exceed customer expectations. Our commitment extends to fostering mutually beneficial relationships with both internal and external customers, local and international suppliers through the effective and full involvement of our people.

The top management of TEKHAF Trading PLC is fully committed to continuously improve the quality of its products and services by implementing ISO 9001:2015 Quality Management System. We conform to Health, Safety, Environment, and Quality (HSEQ) standards and other legal requirements adhering to the following strategies:

a) Delivering high-quality products and services that exceed customer expectations;

b) Expanding business portfolio and develop new products & markets that drive sustainable growth and meet evolving market demands; and

c) Enhancing organizational capabilities, optimizing operational excellence and strengthening relationship with partners and collaborators;

To achieve these strategies, top management will conduct an ongoing awareness campaign to cultivate a strong quality mindset and establish a quality culture within the company. The Quality Policy will be communicated to internal and external stakeholders and shall be applied by all employees of the company.

Approved by:

Mebratu Gowomsa

General Manager 

Dated: March 2024


የጥራት ፖሊሲ

ቴክሃፍ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከደንበኞቹ የሚጠበቅበትን የትራንስፖርት አገልግሎት እና የገቢ ና ወጪ ምርቶች ግብይት ደንበኞችን በላቀ ሁኔታ በሚያረካ መልኩ ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው፡፡ ይኸውም በውስጥ እና በውጪ ላሉ ደንበኞቻችን የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ አቅራቢዎችን ውጤታማ እና የተሟላ የሠራተኞቻችን ተሳትፎ የታከለበትና የጋራ ጥቅምን የሚያበረታታ ነው፡፡

 

የቴክሃፍ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የበላይ አመራር አይኤስኦ 9001 2015ን የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ የምርት እና አገልግሎቱን ጥራት በቀጣይነት ለማሻሻል ቁርጠኛነት አለው፡፡ እንዲሁም ድርጅታችን የሚከተሉትን ስትራቲጄዎች በመከተል የጤና ደህንነት፣ አካባቢ እና ጥራት (ኤች፣ኤስ፣ኢ፣ኪው) እና ሌሎች ሕጋዊ መስፈርቶችን ለማሟላት ይተጋል፡፡

 

ሀ) ደንበኞቹ ከሚጠበቁት የላቀ ጥራት ያላቸው ምርቶች እና አገልግሎት ማቅረብ

ለ) የሥራ ፖርት ፎሎዋችንን በማሳደግ አስተማማኝ የሆነ እድገትን እና የገበያውን ፍላጎት የሚያሟላ አዳዲስ ምርቶች እና ግብይቶች ማጎልበት

ሐ) የድርጅትን አቅም ከፍ ማድረግ ፡ የተመቻቸ የክወና ልቀት እና የአጋሮች እና ተባባሪዎቻችንን ግንኙነት ማጠናከር ናቸው፡፡

እነዚህን ስትራቴጂዎች ለማሳካት የበላይ የሥራ አመራሩ ጠንካራ የጥራት አስተሳሰብ እና ባህልን በድርጅቱ ውስጥ ለመገንባት ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡ የጥራት ፓሊስው ለውስጥ እና ለውጪ ባለድርሻ አካላት የሚገለጽ ሲሆን በሁሉም የድርጅቱ መመሪያ ክፍሎች ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡


ያፀደቀው

መብራቱ ጎዎምሳ

ዋና ስራ አስኪያጅ

መጋቢት 2016 ዓ.ም